Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tg-me/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/orthodox1/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tg-me/post.php on line 50
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 | Telegram Webview: orthodox1/13012 -
Telegram Group & Telegram Channel
« ወልደ ነጐድጓድ  ተሰደ  እንዘ  የኀድግ  ሀገረ፤
እምኅበ  አጥፍአ  ሞተ  ሰብእ  ሦረ፤
ገራህቱ  መቅበርት አምጣነ አብቈለት  ሣዕረ»

ሰ) ከውጭ የተገኙ ቀደምት ምንጮች

በውጭ ሀገራት ቀደምት ድርሳናትና  ሊቃውንትም ዘንድ ቢሆን ከላይ ያነሳነውን ጭብጥ የሚደግፍ ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

https://www.stjohnaz.org/about-us/our-patron-saint/#:~:text=He%20bade%20them%20prepare%20for,disobedient%2C%20they%20fulfilled%20his%20bidding.

     በሌላ ሥፍራ የተገኘው ደግሞ ይህን ይላል ቅዱስ ዮሐንስ የሚነጠቅበት ሠዓት እንደደረሰ ሲያውቅ በመስቀል ቅርጽ የተሰናዳ መቃብር እንዲያዘጋጁለት አርድእቱን አዟል እነርሱም በበዛ እንባ መምህራቸውን እየሳሙ ካለመታዘዝ እንዳይቆጠርባቸው ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ወደ መቃብሩ ሥፍራ አኑረውት ሄደዋል። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ( ቅዱስ አብሮኮሮስ) ወደቦታው ተመልሶ ቢመጣ መቃብሩን ቢከፍተው ባዶ ሆኖ አግኝቶታል።

«He bade them prepare for him a cross-shaped grave, in which he lay, telling his disciples that they should cover him over with the soil. The disciples tearfully kissed their beloved teacher, but not wanting to be disobedient, they fulfilled his bidding. They covered the face of the saint with a cloth and filled in the grave. Learning of this, other disciples of Saint John came to the place of his burial. #When_they_opened_the_grave, they found it empty.»

በአብሮኮሮስ ስለተሠጠው ምስክርነት (testimony of St. Prochorus) ደግሞ ተከታዩት አስረጂ በሊንኩ ታግዘው ቢያዩ የበከጠ ሐሳባችንን ያግዛል።

https://www.johnsanidopoulos.com/2009/09/repose-of-st-john-theologian-according.html?m=1

ከዚህ በዘለለ ጽንፍ አንዳንዶች ደግሞ ዛሬ መቃብሩ ባለበት አጽሙ የማይገኘው  ከጌታችንና ከእመቤታችን ቀጥሎ የትንሳኤ ዘለክብር ባለቤት ሆኖ ዕለተ ምጽኣትን ሳይጠብቅ እሱም ከሙታኑ ተለይቶ የተነሳ  ስለሆነ ነው የሚል ትውፊት አላቸው፤ ይህንንም ትንሳኤ Metastasis እያሉ በመግለጥ ዐመታዊ ዕለተ ትንሳኤውን በወርኃ መስከረም ያከብራሉ! 

According to Holy Tradition, the reason we have no physical remains but rather an empty tomb of the Apostle John is because when the disciples returned to his tomb, it was found empty. It is assumed that he was raised, just like the Lord and the Theotokos. This is what we call "Metastasis" (Translocation or Transposition), and it is what we celebrate on September 26th.

✧ ሞቷል ለሚለውስ በማስታረቂያነት ምን ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል?

በኤፌሶን/ ቱርክ የመቃብሩ ሥፍራ ይህ ነው እየተባለ ዛሬም ለጎብኚዎች ይታያል።
ይሁንና ግን ከላይ እንዳየነው
☞ ገራህቱ  መቅበርት አምጣነ አብቈለት  ሣዕረ ፣
☞ልብሱ ለዮሐንስ ወአሣእኑ ዘተኃድገ ለአብሮኮሮስ  ከመ ያዑቅ ሕይወቱ ፣
☞ When they opened the grave, they found it empty… በማለት መቃብሩ እንጂ የተቀባሪው የከበረ ሥጋ በቦታው አለመገኘቱ ተነግሯል፤  
አስቀድሞ በመላእክት ቢሉ በደቀመዛሙርቱ መቃብሩ መዘጋጀቱ እውነት ቢሆንም ሥጋው ከዚያ መታጣቱና የአብሮኮሮስ ምስክርነት ተሰውሯል ወደሚለው ያደርሰናል።

በአንዳንድ የስንክሳር ቅጂዎችና ድርሳናት  አዕረፈ ☞ ሞተ የሚል  አገላለጥ እናገኛለን ፤ ይህን በሚመለከት ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጥቀዋል ብላ ቤ/ክርስቲያን የምትናገርላቸውን ቅዱሳንን አዕረፈ ብሎ ማስቀመጥ በአያሌው የተለመደ ሆኖ ይታያል። ዐረፈ  የሚለው በአገባቡ ሞትን ብቻ አይገልጥም ከዚህ ዐለም ድካም መለየትን ካለንበት ዓለመ መሬት (ምድር) በሕይወት ወደ ብሔረ ብፁዓን አልያም ብሔረ ሕያዋን መሻገር ዕረፍት፣ ከጣር ከገኣር መለየት ተብሎ ሊነገር  እንደሚችል ማጤን ይገባል።

የሌሎቹን አበው ወደብሔረ ሕያዋን መሔድ ዕረፍት ይለዋል
ለአብነት ግንቦት ፲፩ ስለ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር  «በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው ኢትዮጵያዊው ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ» ይላልና።

ሌላው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያው ግዛቱና ሀገረ ስብከቱ ቁስጠንጥንያ ለኤፌሶን አጎራባች (ዛሬ ሁለቱም በቱርክ ያሉ አውራጃዎች ናቸው) በመሆኑ  የበዛውን የቅዱሳን አጽማቸው የት እንዳለ አናውቅም ነገር ግን የታወቁ የቅዱስ ጴጥሮስ የቅዱስ ጳውሎስ የቅዱስ ቶማስና የቅዱስ ዮሐንስ መቃብራቸው በእኛ ዘንድ አለ ሲል በ፳፮ኛው ድርሳኑ ላይ አስፍሯል  «እስመ መብዝኅተ አዕፅምቲሆሙ ለሐዋርያት ኢነአምር አይቴ ውእቱ ወዘያሌቡሰ ላዕለ ዝንቱ ከመ መቃብረ  ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ ወቶማስ  እሙራን ወክሡታን እሙንቱ»

ታላቁ ቆስጠንጢኖስ በዘመኑ ከፈጸማቸው ደገኛ ተግባራት አንዱ አጊዮ አፖስቶሊ (Ἅγιοι Ἀπόστολοι) የሚባለውን
የቅዱሳን ሐዋርያት መካነ መቃብር  ያለበት ቤተመቅደስ ገንብቶ የሁሉንም ሐዋርያት አጽማቸውን በአንድ ቦታ ለመሰብሰብ ጥረት አድርጎ ነበር፤  ይሁንና ግን የቅዱስ እንድርያስና  የቅዱስ ሉቃስ እንዲሁም የቅዱስ ጢሞቴዎስ ብቻ ሥጋ በቦታው ለማኖር ችሏል። መቃብራቸው ቢገኝም ተቀባሪዎቹ አለመገኘታቸውን ማወቅ ይገባል።

እንደመውጫ ቅዱስ ዳዊት  “ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?”  ይላል【መዝ ፹፱ ፥፵፰ 】ከሰው ወገን ሕያው ሆኖ ለዘለዓለም ነዋሪ ሞትንም ሳያይ በምድር ላይ ቀሪ የሆነ ማንም የለም። የሐዋርያው ክብርና ቅድስናም ከመሞቱ  አልያም ወደ ብሔረ ሕያዋን ከመነጠቁ ጋር በቀጥታ የሚያያዝበት ልኬት የለውም። ባለመሞቱ የሚከብርበት በመሞቱ የሚቀርበት መንገድ ስለሌለ ክርስቶስ አይሞትም አላለም እስክመጣ ቢኖር…  አለ እንጂ።
ሰው ሕያዊት ነፍሱበ በሞት ከተለየችው እንደፈሰሰ ውኃ ነው
ፈሶ የታፈሰ ውኃ 【ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ】
የቅዱሱ መጽሐፍ ብሂል እንዲህ ይላል "ዘእምከመ ተክዕወ ማይ ውስተ ምድር ኢይትገባእ" እኛም እንጂ ይህን ይዘን «የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም» እንል የለ!?
【፪ኛ ሳሙ፲፬፥፲፬ 】
ዮሐንስ ግን ሞቶ ተቀበረ ሲሉት ተነስቶ የተነጠቀ ነውና የታፈሰ ውኃ ነውና "ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ" አልነው።

ሞተ የተባለ በሰዎች ኅሊና የተቀበረውን ማንነታችን ወደልዕልናው በቸርነቱ ይንጠቅልን

ሎቱ ስብሐት ለዘበስብሐተ አቡሁ ይሴባሕ፤  ወሎቱ ቅድሳት
ለዘበቅድሳተ መንፈሱ ይትቄደስ 🙏

☞  Edited & Яερõšтεδ ƒrõ๓ ጥር ፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.

tg-me.com/orthodox1/13012
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodox1/13012

View MORE
Open in Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

That strategy is the acquisition of a value-priced company by a growth company. Using the growth company's higher-priced stock for the acquisition can produce outsized revenue and earnings growth. Even better is the use of cash, particularly in a growth period when financial aggressiveness is accepted and even positively viewed.he key public rationale behind this strategy is synergy - the 1+1=3 view. In many cases, synergy does occur and is valuable. However, in other cases, particularly as the strategy gains popularity, it doesn't. Joining two different organizations, workforces and cultures is a challenge. Simply putting two separate organizations together necessarily creates disruptions and conflicts that can undermine both operations.

What is Telegram Possible Future Strategies?

Cryptoassets enthusiasts use this application for their trade activities, and they may make donations for this cause.If somehow Telegram do run out of money to sustain themselves they will probably introduce some features that will not hinder the rudimentary principle of Telegram but provide users with enhanced and enriched experience. This could be similar to features where characters can be customized in a game which directly do not affect the in-game strategies but add to the experience.

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 from us

Telegram ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
FROM USA